ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰባት ዐበይት ምሥጢራት ምእመናን ታገለግላለች፤ ምሥጢራት የተባሉበትም ምክንያት በዓይናችን ልናያቸው በእጃችን ልንዳስሳቸው የማንችል ልዩ ልዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታወዎች በእነዚሁ ምሥጢራት አማካይነት የሚሰጡን ስለሆነ ነው፡፡
ሰባቱ ምሥጢራት፡-
- ምሥጢረ ጥምቀት
- ምሥጢረ ቅብዓተ ሜሮን
- ምሥጢረ ቁርባን
- ምሥጢረ ክህነት
- ምሥጢረ ተክሊል
- ምሥጢረ ንስሐ
- ምሥጢረ ቀንዲል ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዕማድ ምሳሌነት በምሳሌ ሰሎሞን የተነገረውን መነሻ በማድረግ ምሥጢራት ሰባት መሆናቸውን ትቀበላለች (ምሳ. 9፥1)፡፡ እነዚህ ሰባት ምሥጢራት በሚታየውና በሚዳሰሰው በግዙፉ አካል አማካይነት ረቂቁን የማይታየውንና የማይዳሰሰውን የእግዚአብሔርን ጸጋ ለምእመናን የምታሳትፍባቸው ናቸው፡፡ ከእነዚሀ ሰባት ምምጢራት ስድስቱ በጳጳስም፣ በቄስም የይፈጸማሉ፣ የክህነትን ሥልጣን መስጠተ ግን የሚፈጸመው በጳጳስ ብቻ ነው፡፡
- ምሥጢረ ጥምቀት
ጥምቀት ከሰባቱ ምሥጢራት የመጀመሪያው ነው፡፡ ጥምቀት ዳግመኛ ተወልደን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የምንገባበት ምሥጢር ነው፡፡ (ዮሐ.3፥5)፡፡ ጥምቀት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትእዛዝ አለው፡፡ (ማቴ.28፥19-20)፡፡
በጥምቀት ኃጢአት ይሠረያል (የሐዋ.ሥራ 2፥8)፡፡ መንጻትና መቀደስም በጥምቀት ነው፡፡ (1ጴጥ.፥3:21፣ ቲት.3፥5-6)፡፡
በቤተ ክርስቲያናችን ሕፃናትን እናጠምቃለን፡፡ በብሉይ ኪዳን ሕፃናት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚኖራቸው በተገረዙ ጊዜ ነበር፤ በሐዲስ ኪዳንም ሕፃናት በሕፃንነት ዕድሜሜቸው ተጠምቀው የክርስቶስ ቤተሰቦች ስለሚሆኑ በሕፃንነት ይጠመቃሉ፤ እግዚአብሔር ሕፃናትን ከጸጋው ለይቷቸው አያውቅም፤ ለምሳሌ ኤርምያስ የተቀደሰው በእናቱ ማኅፀን ነበር፡፡ (ኤር.1፥5)፡፡ ዮሐንስ መጥምቁም በእናቱ ማኅፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ተመልቶ ነበር፡፡ (ሉቃ.1፥15)፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን በማስተማር ዘመኑ ሕፃናትን ባርኳቸዋል ይህም ሕፃናት ዕድሜያቸው ወደ እግዚአብሔር ከመቅረብ የሚከለክላቸው አለመሆኑን ያሳያል፡፡ (ማቴ.19፥13-15፤ ማር.10፥13-15፤ ሉቃ.18፥15-17፣ የሐዋ. ሥራ 16፥33፣ 1ቆሮ. 1፥16)፡፡
በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት ወንድ ልጅ ሲወለድ በዐርባ ቀን፣ ሴት ልጅ ስትወለድ በሰማኒያ ቀን ይጠመቃሉ፡፡ በብሉይ ኪዳን ወንድ ልጅ በተወለደ በዐርባ ቀኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት ይገባ ነበር፤ ሴት ልጅ ስትወለድም በሰማንያ ቀኗ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትገባ ነበር፡፡ (ዘሌ.12፥15፣ ሉቃ.2፥21-24)፡፡ ሕፃናት ሃይማኖታቸውን ለመመስከር ስለማይችሉ ለወንድ ሕፃን የክርስትና አባት ለሴቲቱ ሕፃን የክርስትና እናት ይሰየሙላቸዋል፡፡ ጥምቀት በመዝፈቅ ነው፡፡ ጥምቀት በሥላሴ ስም ነው፡፡ (ማቴ.28፥19-20)፡፡ ከመጠመቃቸው አስቀድሞ ለክርስቶስ ሲሉ በሰማዕትነት ደማቸውን ያፈሰሱ ሰማማታትም በደማቸው እንደተጠመቁ ይቈጠራሉ፡፡ (ማቴ.10፥32፣ 16፥25)፡፡
ሥርዓተ ጥምቀት
- ጥምቀት ውሃ በብዛት ከሚፈስበት ጥምቀተ ባሕር (በወንዝ) ይፈጸማል፡፡
- በቤተ ክርስቲያን ብዛት ያለው ውሃ ካልተገኘ በቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ኩሬ በማበጀት ወይም ሰፊ ገንዳ በመሥራት ሰውነትን በሙሉ ሊያጠልቅ በሚችል ውሃ ይፈጸማል፡፡
- ተጠመማቂው የሚያጠልቅ ውሃ በማይገኝበት ስፍራ የተገኘውን ውሃ ሦስት ጊዜ በእጅ ታፍነው ወየም በጽዋዕ ቀድተው መላ ሰውነቱን እንዲነካው በማድረግ ያጠምቋል፡፡ (ዲድስቅልያ 34፡፡ ፍት.ነገ. አንቀጽ 3)፡፡
- ካህኑ የጥምቀቱን ጸሎት ከፈጸመ በኋላ ተጠማቂውን ይዞ “አሰግደከ/ኪ/ ለአብ፣ አሰግደከ/ኪ/ ለወልድ፣ አሰግደከ/ኪ/ ለመንፈስ ቅዱስ – ለአብ እንድትሰግድ/ጂ/ አደርጋለሁ፣ ለወልድ እንድትሰግድ/ጂ/ አደርጋለሁ፣ ለመንፈስ ቅዱስ እንድትሰግድ/ጂ/ አደርጋለሁ” እያለ በዐራቱ መዓዝን ያሰግደዋል፡፡ ሲያጠምቅም “አጠምቀከ/ኪ/ በአብ፣ አጠምቀከ/ኪ/ በወልድ፣ አጠምቀከ/ኪ/ በመንፈስ ቅዱስ” እያለ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ያጠምቃል፡፡ (ማቴ.28፥19-20)፡፡
- ተጠማቂው ወደ ጥምቀት ሲቀርብ ጠጉሩን ይላጫል ልብሱን ያወልቃል፡፡
- ተጠማቂው ከተጠመቀ በኋላ ወዲያውነ ተቀድሶ ሥጋውንናa ደሙን ይቀበላል፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት ቅዱስ ቁርባን የምሥጢራት ሁሉ መደምደሚያ ስለሆነ ነው፡፡
- ተጠማቂዎቹ አዋቂዎች ከሆኑ የተወሰነ የትምህርት ጊዜ ተሰጥቶ መሠረተ እምነት እንዲማሩና ዐውቀው አምነው እንዲጠመቁ ይደረጋል፡፡
- ወንዶች ወንዶችነን፣ ሴቶችም ሴቶችን ብቻ ክርስትና ያነሣሉ፡፡ (ፍት.ነገ.አን.3፣ ዲድስቅ.34፣ ዘኒቅ 24)፡፡
- ማንኛውም ሰው ለመጠመቀ ከተወሰነው ጊዜ በፊት ለሞት የሚያሰጋ ሕመም ቢደርስበት ሥርዐተ ጥምቀት ይፈጸምለታል፡፡ (ፍት.ነገ.አን.3)፡፡
- ተጠማቂዎች ተምረው ዐውቀው የመሚጸልዩ ከሆነ ራሰሳቸው የማይችሉ ከሆነ የክርስትና አባቶች ወይም እናቶች ጸሎተ ሃይማኖትን እንዲጸልዩላቸው ይደረጋል፡፡ ትምህርተ ሃይማኖትንም አያስተማሩ ለማሳደግ ቃል ይገባሉ፡፡
- ከክርስቲያን ቤተሰብ የሚወለዱ ሕፃናት ወንዶች በ40 ቀን ሴቶች በ80 ቀን ይጠመቃለ፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ሰው በክርስቶስ አዳንነት ከአመነ በማኝኛውም ዕድሜ ከመጠመቅ አይከለከልም፡፡
- ጥምቀት በሥላሴ ስም ነው፡፡ (ማቴ.28፥19)፡፡
- ጥምቀት አይደገምም (ሮሜ 6፥3-4፤ ኤፌ. 4፥4-7)፡፡
- ጥምቀት በውሃ ብቻ ነው፡፡ (ዮሐ.3፥5፣ ፍት.ነገ.3)፡፡
- ተጠማቂው ከተጠመቀ በኋላ ማተብ በአንገቱ ይታሰርለታል ይህም የክርስቲያን ምልክትና መለያ ነው፡፡ ጥምቀት የክርስቶስ ሞት ምሳሌ ነው፤ የክርስቶስ ሙቶ መቀበር ተጠማቂው ወደ ማጥመቂያው ለመግባቱ ምሳሌ ሲሆሆ ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ በመነሣቱ ደግሞ ተጠማቂው ትንሣኤ ዘለክብርን የሚነሣ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ (ዲድስቅ 34፣ ሮሜ 6፥5-6)፡፡ ከዚህም ጋር ጥምቀት በመጽሐፈ ክርስትናና በፍትሐ ነገሥት በተወሰነው መሠረት ይፈጸማል፡፡
- ምሥጢረ ሜሮን
ተጠማቂው ከማጥመቂያው ሲወጣ ሚቀባው ቅዱስ ዜት ነው፡፡ ሜሮን እንደ ጥምቀት ነው፤ አይደገምም፡፡ በቅብዐተ ሜሮን ተጠማቂው የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ይቀበላል፡፡ በሐዋርያት ጊዜ አማኞች ከተጠመቁ በኋላ በአንብሮተ እድ መንፈስ ቅዱስን ያሳድሩባቸው ነበር፡፡ (የሐዋ. ሥራ 20፥14-17)፡፡ ቤተ ክርስቲያን እየተስፋፋች በሔደች ጊዜ ግን በአንብሮተ እድ ፈንታ በሐዋርያት መንበር የተተኩ ኤጲስ ቆጶሳት በቅዱስ ሲኖዶስ ሜሮን እያዘጋጁ አዲስ የተጠመቀ ሁሉ እንዲታተምበት ፈቀዱ፡፡
በሜሮን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያ ነው
ሜሮን የሚቀባው ተጠማቂው ወዲያው ከማጥመቂያው ሲወጣ ነው፡፡ ሐዋርያት ሕፃኑንም ሆነ ሽማግሌውን ወዲያው በአንብሮተ እድ መንፈስ ቅዱስን ያሳድሩበት ነበር፡፡ (ሐዋ. 8፥14-17፤ 19፥5-6)፡፡ ሕፃናት ከተጠመቁ በኋላ መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ወዲያውኑ በሜሮን ይቀባሉ፡፡ እንኳን ተወልደው በእናታቸው ማኅፀን ሳሉ በመንፈስ ቅዱስ የከበሩ ሕፃናት እንዳሉ መጽሀፍ ቅዱስ ይመሰክራል፡፡ (ሉቃ.1፥15፣ ኤር. 1፥1-8)፡፡ ሜሮን የመቅባት ሥልጣን ያለው በሐዋርያት መንበር የተቀመጠው ኤጲስ ቆጶስ ነው፡፡ ቄሶችም እንዲቀቡ ተፈቅዷል፡፡
3. ምሥጢረ ቁርባን
በቤተ ክርስቲያናችን የምሥጢራት ሁሉ መደምደሚያ ቅዱስ ቁርባን ነው፡፡ ቁርባን ማለት መሥዋዕት ማለት ነው፡፡ ይኸውም ሰው ለእግዚአብሔር ያቀረበው ሳሳሆነ እግዚአብሔር ስለሰው ያቀረበው ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን በምኵራብ የተሠዋው በግና ፈየል ሁሉ በአዲስ ኪዳን በቤተ ክርስቲያን ለሚሠዋው የክርስቶስ ሥጋና ደም ምሳሌ ነበር፡፡ መልከ ጼዴቅ ለአብርሃ ያበረከተው ኅብስተ አኰቴት ጽዋዐ በረከት፡፡ (ዘፍ.14፥18)፡፡ እስራኤል የነጻነታቸው ዕለት የሠዉት መሥዋዕት የፋሲካችን በግ የክርስቶስ ሥጋ ምሳሌ ነበር፡፡
ቁርባን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት አለው፡፡ (ማቴ.26፥26፣ 1ቆሮ.11፥23-25)፡፡ ቄሱ ኅብስቱን በጻሕል ወይኑን በጽዋዕ አድርጎ ጸሎተ ቅዳሴውን ሲያደርስ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ፣ ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት ይሆናል፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ለምእመናን የምናቀብለው ከሥጋውም ከደሙም ነው፡፡ (ዮሐ.6፥54-58፣ ማቴ.26፥27)፡፡
ቄሱ ሥጋውን ሲያብል ዲያቆኑ ደሙን በዕርፈ መስቀል ያቀብላል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን መምጣት ለማይችሉ በሽተኞች በዕለቱ ተቀድሶ በቤታቸው እንዲቈርቡ ይደረጋል፡፤ መሥዋዕቱ ከዕለቱ አያልፍም፤ አይውልም፤ አያድርም፡፤ ቁርባን የሚማረበው ሳይበላ ሳይጠጣ ቢያንስ ለ15 ሰዓት በመጾም ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ቁርባን ፍጹም የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው፡፡ (ዮሐ.6፥51-55)፡፡
እንደ ሌሎቹ ምሥጢራት ሁሉ ቁርባን የሚፈጽሙ በሐዋርያት መንበር የተቀመጡ ጳጳሳት ነበሩ፡፡ ቤተ ክርስቲያን እየተስፋፋች ስትሔድ ግን ለቀሳውስት ፈቀዱላቸው፤ ዲያቆናት የጳጳሱና የቄሱ ረዳቶች ናቸው፡፡ ራሳቸውን በንሰሓ ያላዘጋጁ ግን ቢቀበሉ ዕዳ ይሆንባቸዋል፡፡ (1ቆሮ.11፥28-29፣ ዮሐ. አፈ ወርቅ ቅዳሴ)፡፡
- ምሥጢረ ክህነት
ክህነት የቤተ ክርስቲያ ከፍተኛው መንፈሳዊ መዐርግ ነው፡፤ ክህነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት አለው፡፡ (ማቴ.28፥19፣20፣ ኤፌ.4፥11፣ የሐዋ፣ሥራ 28፥20)፡፡
በቤተ ክርስቲያናችን የክህነት መዐርጋት ሦስት ናቸው፤ እነሱም ዲቁና፣ ቅስናና ጵጵስና ናቸው፡፡
1ኛ ዲያቆን
ሀ. ከማግባቱ በፊት ደዲቁና ይሾማል፡፡
ለ. አግብቶ ወይም መንኩሶ የቅስና መዐርግ ይቀበላል፡፡
ሐ. አገልግሎቱም የቄስና የጳጳስ ረዳትነት ነው፡፡
መ. የሚሾመው በጳጳስ ነው፡፡
ሠ. በቤተ ክርስቲያናችን ከሙሉ የዲቁና መዐርግ በፊት ለተልእኮ የሚያበቁ 3 መዓርጋት የሚሰጡ በአንብሮተ እድ ሳይሆን በቃለ ቡራኬ ብቻ ነው፡፡
ረ. ዲያቆናት በአንብሮተ እድ ብቻ ይሾማሉ፡፡
ሰ. ሥልጣነ ክህነት ለመmቀበል ዋጋ አይሰጥም፡፡ (የሐዋ.ሥራ 8፥18-26)፡፡
ሸ. ክህነት በዘር ሐረግ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ጥሪና በቤተክርስቲያን ቀኖና ነው፡፡
2ኛ ቄስ
ዲያቆኑ ካገባ በኋላ ወይም ከመነኮሰ በኋላ የቅስና ሥልጣን ይቀበላል፡፡ አገልግሎቱም ሥልጣነ ክህነት ከመስጠት ሜሮን ከማዘጋጀት አዲስ ቤተ ክርስቲያንና አዲስመንንር አዲስ ጽላትና ሌሎችንመ አዳዲስ ንዋየ ቅድሳት ከመባረክ በቀር ሌላውን ሀሉ ይፈጽማል፡፡
በድንግልና የቀሰሰ ከሆነ ወደ ጵጵስና መዐርግ መድረስ ይችላል፡፡ ባለ ሕገ ከሆነ ግን በዚህኛው መዐርግ ብቻ ይወሰናል፡፡ ይይም በአንብሮተ እድና በንፍሐት በጳጳስ ይሾማል፡፡
3ኛ ጳጳስ (ኤጲስ ቆጶስ)
ኤጲስ ቆጶስነት የሚሾመው በደንግልና የመmነኮሰ ካህን ነው፡፡ የሚሾመው በመላ የሲነዶስ አባላት ነው፡፡ በችግር ጊዜ ግን ከሁለት ባላነሱ ኤጲስ ቆጶሳት በአንብሮተ እድና በንፍሐትe ይሾማል፡፡ አገልግሎቱም ምሥጢራትን ከመፈጸም ጋር ጠቅላላ የቤተ ክረስቲያን መሪና ጠባቂ ነው፡፡ እነዚህን መዐርጋት የሚቀበሉ ሁሉ የሚያሟሏቸው ግዴታዎች አሏቸው፡፡
ሀ. ጤንነት ያላቸው
ለ. ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋት በቂ ትምህርት ያላቸው
ሐ. በጠባይ የተመሰገኑ መሆን አለባቸው
መ. ወደ መዐርገ ከህነት የሚቀርቡ ሁሉ በቤተ ከክርስቲያናችን ሥርዓት ወንዶቸች ብቻ ናቸው፡፡
ሠ. ክህነት አይደገምም ወየይም አይታደስም በድጋሚ ክህነት የሚቀበል ወይም የሚሰጥ ሁለቱም ከክህነታቸው ይይራሉ፡፡ (የሐዋርያ ቀኖና 68)፡፡ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን የተወሰኑ ሰዎችን ለክህነት መርጦአል፡፡ (ሉቃ.6፥12፣ 13፡ ዮሐ. 20፥19-25)፡፡ ለሌላ ያልተሰጠ ልዩ ሥልጣንም ሰጣቸው፡፡ (ማቴ.18፥18)፡፡ በዕርገት ሲሰናበታቸው እስከ ዓለም ፍጻሜ እንደማይለያቸው ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ (ማቴ.28፥20)፡፡ ሲያርግም ጠቅላላ መዐርገ ክህነትን ሾሟቸው ዐረገ፡፡ (ሉቃ.24፥51)፡፡
ከሐዋርያት አባልነት በወጣው በይሁዳ ምትክ ለመምረጥ በሲኖዶስ ተሰብስበው ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማትያስን መምረጣቸው የሐዋርያት አxገልግሎት ከሌላው ሕዝባዊ አገልግሎት የተለየ መሆኑን ያሳያል፡፡ (የሐዋ. ሥራ 1፥15-26)፡፡
- ምሥጢረ ተክሊል
የክርስቲያኖች ጋብቻ በቤተ ክርስቲያን ምስክርነት የሚፈጸም ጸጋ መንፈስ ቅዱስንም የሚያሰጥ ስለሆነ ከሰባቱ ምሥጢራት አንዱ ነው፡፡ ጋብቻ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት አለው፡፡ (ዘፍ.1፥27፣ 2፥18፤ ማቴ.19፥4-6)፡፡ በቤተክርስቲያናችን ቀኖና መሠረት ክርስቲያናዊ ጋብቻ ከመፈጸሙ በፊት የሚከተሉት ግዴታዎች መሟላት አለባቸው፡፡
- ጸጋ መንፈስ ቅዱስን በእኩልነት የሚቀበሉ ስለሆኑ ሁሉም ክረrስቲያን መሆን አለባቸው፡፡
- ሁለቱም የኦረቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባላት መሆን አለባቸው፡፡
- ሁለቱ አንድ ካልሆኑ ግን ጋብቻው ከመፈጸሙ በፊት የቤተ ክርስቲያናችን አባል መሆን ግዴታ ነው፡፡
- ከጋጋቻ በፊት ሥጋዊ ግንኙነት ኤፈቀድም፡፡
- ለጋብቻው ሁለቱም ፈቃደኞቸ መሆን አለባቸው፡፡
- በቤተሰብ መካከል የሥጋዊውም ሆነ መንፈሳዊ ተዘምዶ ገደብ በጋብቻ እንዳይፈርስ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ መከበር አለበት (ዘሌ.18፥6-21፣ ዘዳ.7፥3-4)፡፡
- በሞት በዝሙት ካልሆነ በቀር ከሁለቱ አንዱ ተለይቶ ለማግባት አይችልም (ማቴ.19፥6፣9)፡፡
- የክርስቲያኖች ጋብቻ የክርስቶስና የቤተክርስቲያን አንድነት ምሳሌ ስለሆነ አይፈርስም፡፡ (ኤፌ.5፥32)፡፡
- የተክሊልን ምሥጢር የሚፈጽሙ ጳጳሳትና ቀሳውስት ናቸው፡፡
- ተክሊል ያለ ሥጋ ወደሙ አይፈጸምም፡፡ (ፍት.መን.24፣ ቁ899)፡፡
- በጋብቻ ጊዜ የወላጆች ፈቃድ መጨመር አለበት፡፡
- ምሥጢረ ንስሐ
ንስሐ ማለት መጸጸት፣ መመለስ፣ ከኃጢአት መንጻት ማለት ነው፡፡ ክርስቲያኖች በጥምቀት እንደገና የተወለዱ ቢሆኑም፣ ሰው ሆኖ ወደ ኃጢአት ማዘንበል የማይቀር ነውና እያንዳንዱ ክርስቲያን መምህረ ንስሐ ሊኖረው ይገባል፡፡
ክርስቲያኖች ወደ መምህረ ንስሓ እየሄዱ ኃጢአታቸውን ይናዘዛሉ፡፡ (ዘሌ.14፥31፣ ማቴ.8፥4፤ ኤጲፋንዮስ ሃይ. አበው ምዕ.59 ቁ 20)፡፡ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ያደረጉት ሙከራና ኃጢአታቸውን መናዘዛቸው ጸጋ እግዚአብሔርን ያሰጣቸዋል፡፡ ሥጋውን ደሙን ተቀብለው ወደ ቀደመ ክብራቸው ይገባሉ፡፡
ኑዛዜ መቀበልና ማስተሥረይ የሚገባቸው ጳጳሳትናa ቀሳወውስት ብቻ ናቸው፡፡ ንስሐሓ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት አለው፡፡ (ማቴ.8፥4፣ 16፥19)፡፡ ንስሐ ተነሳሒው በመምህረ ነስሓው ፊት ቀርቦ ኃጢአቱን በመናዘዝ የሚያፈሰው ዕንባ የኃጢአቱን ክብደደት እያስታወሰ የሚያሳየው ጭንቀት በመንፈስ ቅዱስ እንደገና እንዲታደስ ያደርገዋል፡፡ (የአትናቴዎስ ቅዳሴ)፡፡
ንስሐ ከሚደጋገሙ ምሥጢራት አንዱ ነው፡፡ ከነቢያተ ጀምሮ የመጥምቁ ዮሐንስ፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስና የተከታዮቹ የሐዋርያት የትምህርት ዋና ዓላማ ሰው ሁሉ በንስሓ እንዲመለስና ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲገባ “መንግሥተ ሰማያተ ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” የሚል ነበር፡፡ ዛሬም ቤተ ክርስቲያን ስለ ንስሓ የምታስተምረው ይህንኑ መሠረት አደድረጋ ነው፡፡ (ዘካ. 1፥3፣ ማቴ.3፥1-2፣ 4፥17)፡፡
- ምስጢረ ቀንዲል
ቀንዲል ቤተ ክርስቲያናችን ከምትገለገልባቸው ሰባት ምሥጢራት አንዱ ነው፡፡ ይህ ምሥጢረ ቀንዲል ለበሽተኞች የሚቀባ ነው፡፡ ቀንዲል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት አለው፡፡ (ማቴ.6፥13፤ ያዕ.5፥13-15)፡፡
በቤተ ክርስቲያናችን የቀንዲል መድኃኒትነት ለሥጋ ብቻ ሳይሆን ለነፍስም ስለሆነ በኃጢአት ደዌ ለተያዘ ቀንዲል ይደረግለታል፡፡ የቀንዲል ምሥጢር የሚፈጸመው በጳጳሳትና በቀሳውስት ነው፡፡
ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ለእያንዳንዳቸው የሚፈጸም የየራሳቸው የሆነ መጽሐፈ ጸሎትና የአፈጻጸም ሥርዐት አላቸው፡፡ ሁሉም ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዐተ አምልኮ ማስፈጸሚያ የሃይማኖት መመሪያ ነው፡፡
እነዚህ ምሥጢራት ሁሉም በቤተ ክርስቲያን ይፈጸማሉ፤ ሆኖም እንደእየሁኔታወ በሌላም ቦታ ይፈጸማሉ፤ ውግዘት የለበትም፡፡ የሁሉም ምሥጢራት ዋና ዓላማ ሰውን ለማዳን ነው፡፡
ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ የአምልኮ ሥርዓት እና የውጭ ግንኙነት